መዝሙር 130:1-8

  • “ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ”

    • “አንተ ስህተትን የምትከታተል ቢሆን ኖሮ” (3)

    • በይሖዋ ዘንድ ይቅርታ አለ (4)

    • “ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ” (6)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 130  ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ።+  2  ይሖዋ ሆይ፣ ድምፄን ስማ። ጆሮዎችህ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና በትኩረት ያዳምጡ።  3  ያህ* ሆይ፣ አንተ ስህተትን የምትከታተል* ቢሆን ኖሮ፣ይሖዋ ሆይ፣ ማን ሊቆም ይችል ነበር?+  4  በአንተ ዘንድ በእርግጥ ይቅርታ አለና፤+ይህም ሰዎች አንተን እንዲፈሩ* ያደርጋል።+  5  ይሖዋን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁለንተናዬ በእሱ ተስፋ ያደርጋል፤*ቃሉን በትዕግሥት እጠብቃለሁ።  6  ንጋትን ከሚጠባበቁ፣አዎ፣ ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይበልጥይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።*+  7  እስራኤል ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ፤ይሖዋ በፍቅሩ ታማኝ ነውና፤+ሕዝቡንም ለመዋጀት ታላቅ ኃይል አለው።  8  እስራኤልን ከበደላቸው ሁሉ ይዋጃል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “በትኩረት የምትመለከት።”
ወይም “ለአንተ አክብሮታዊ ፍርሃት እንዲያድርባቸው።”
ወይም “ነፍሴ በእሱ ተስፋ ታደርጋለች።”
ወይም “ነፍሴ ይሖዋን በጉጉት ትጠባበቃለች።”