መዝሙር 33:1-22
33 እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ።+
ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው።
2 ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት።
3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤+በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ።
4 የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤+ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው።
5 ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል።+
ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።+
6 ሰማያት በይሖዋ ቃል፣በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ* ተሠሩ።+
7 የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤+የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል።
8 መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ።+
የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።*
9 እሱ ተናግሯልና፣ ሆኗል፤+እሱ አዟል፤ ደግሞም ተፈጽሟል።+
10 ይሖዋ የብሔራትን ሴራ* አክሽፏል፤+የሕዝቦችን ዕቅድ* አጨናግፏል።+
11 ይሁንና የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤*+የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።
12 ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።+
13 ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።+
14 ከመኖሪያ ቦታው ሆኖበምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል።
15 የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።+
16 በሠራዊት ብዛት የዳነ ንጉሥ የለም፤+ኃያል ሰው በታላቅ ኃይሉ አይድንም።+
17 ፈረስ ያድነኛል* ብሎ መታመን ከንቱ ተስፋ ነው፤+ታላቅ ኃይሉ ለመዳን ዋስትና አይሆንም።
18 እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤+
19 ይህም እነሱን* ከሞት ለመታደግ፣በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።+
20 ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን።*
እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።+
21 ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።+
22 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን ስንጠባበቅ፣+ታማኝ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “እስትንፋስ።”
^ ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት ያሳዩት።”
^ ወይም “ምክር።”
^ ወይም “ሐሳብ።”
^ ወይም “ምክር ለዘላለም ይጸናል።”
^ ወይም “ድል ያጎናጽፈኛል።”
^ ወይም “ነፍሳቸውን።”
^ ወይም “ነፍሳችን ይሖዋን በተስፋ ትጠባበቃለች።”