መዝሙር 38:1-22
የዳዊት ማህሌት፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።
38 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤ተናደህም አታርመኝ።+
2 ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭኖኛል።+
3 ከቁጣህ የተነሳ መላ ሰውነቴ ታመመ።*
ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።+
4 የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤+እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል።
5 ከሞኝነቴ የተነሳቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ።
6 በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ።
7 ውስጤ ተቃጠለ፤*መላ ሰውነቴ ታመመ።+
8 ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ።*
9 ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
10 ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል።+
11 ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ።
12 ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔን መጉዳት የሚፈልጉም ስለ ጥፋት ያወራሉ፤+ቀኑን ሙሉ ተንኮል ሲሸርቡ ይውላሉ።
13 እኔ ግን እንደ ደንቆሮ አልሰማቸውም፤+እንደ ዱዳም አፌን አልከፍትም።+
14 መስማት እንደማይችል፣በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ።
15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በተስፋ ተጠባብቄአለሁና፤+ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተም መልስ ሰጥተኸኛል።+
16 “በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና።
17 ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም።+
18 በደሌን ተናዘዝኩ፤+ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር።+
19 ይሁንና ጠላቶቼ ብርቱዎችና* ኃያላን ናቸው፤*ያላንዳች ምክንያት የሚጠሉኝ ተበራከቱ።
20 ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር።
21 ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ።
አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+
22 አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “በሥጋዬ ላይ ጤነኛ ቦታ የለም።”
^ ቃል በቃል “መላ ወገቤ ተቃጠለ።”
^ ወይም “እጮኻለሁ።”
^ ወይም “ነፍሴን።”
^ ቃል በቃል “ሕያዋንና።”
^ “ይሁንና ከመሬት ተነስተው የሚጠሉኝ ብዙ ናቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።