መዝሙር 48:1-14

  • ጽዮን፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ

    • “የምድር ሁሉ ደስታ” (2)

    • ከተማዋንና ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ (11-13)

መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። 48  ይሖዋ ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።  2  በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣+በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።+  3  አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥአስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።+  4  እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤*አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ።  5  ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ። ደንግጠውም ፈረጠጡ።  6  በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው።  7  የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ።  8  የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል። አምላክ ለዘላለም ያጸናታል።+ (ሴላ)  9  አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነንስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።+ 10  አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህምእስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል።+ ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።+ 11  ከፍርድህ የተነሳ የጽዮን ተራራ+ ደስ ይበላት፤የይሁዳ ከተሞችም* ሐሴት ያድርጉ።+ 12  በጽዮን ዙሪያ ሂዱ፤ በዙሪያዋም ተጓዙ፤ማማዎቿን ቁጠሩ።+ 13  የመከላከያ ግንቦቿን*+ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ። 14  ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና።+ እስከ ወዲያኛው* ይመራናል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በቀጠሮ ተገናኝተዋልና።”
ቃል በቃል “ሴቶች ልጆችም።”
ወይም “የማይደፈሩ ግንቦቿን።”
“እስክንሞት ድረስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።