መዝሙር 54:1-7
-
ዳዊት በጠላቶቹ መካከል ሳለ እርዳታ ለማግኘት ያቀረበው ጸሎት
-
“አምላክ ረዳቴ ነው” (4)
-
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዚፍ ሰዎች ወደ ሳኦል መጥተው “ዳዊት እኛ ጋ ተደብቋል” ባሉት ጊዜ ዳዊት የዘመረው መዝሙር።+
54 አምላክ ሆይ፣ በስምህ አድነኝ፤+በኃይልህም ደግፈኝ።*+
2 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+ለአፌም ቃል ትኩረት ስጥ።
3 ባዕዳን በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤ጨካኝ ሰዎችም ሕይወቴን* ይሻሉ።+
ስለ አምላክ ምንም ግድ የላቸውም።*+ (ሴላ)
4 እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤+ይሖዋ እኔን* ከሚደግፉ ጋር ነው።
5 የገዛ ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ ይመልስባቸዋል፤+በታማኝነትህ አስወግዳቸው።*+
6 ለአንተ በፈቃደኝነት መሥዋዕት አቀርባለሁ።+
ይሖዋ ሆይ፣ መልካም ነውና፣ ስምህን አወድሳለሁ።+
7 ከጭንቅ ሁሉ ያድነኛልና፤+ጠላቶቼንም በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ተሟገትልኝ።”
^ ወይም “ነፍሴን።”
^ ወይም “አምላክን በፊታቸው አላደረጉትም።”
^ ወይም “ነፍሴን።”
^ ቃል በቃል “ዝም አሰኛቸው።”