መዝሙር 87:1-7
-
ጽዮን፣ የእውነተኛው አምላክ ከተማ
-
በጽዮን የተወለዱ (4-6)
-
የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት።
87 የአምላክ ከተማ የተመሠረተችው በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው።+
2 ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ሁሉ ይበልጥየጽዮንን በሮች ይወዳል።+
3 የእውነተኛው አምላክ ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች እየተነገሩ ነው።+ (ሴላ)
4 እኔን ከሚያውቁኝ* መካከል ረዓብንና*+ ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ኢትዮጵያን* ጨምሮ ፍልስጤምና ጢሮስም ይገኙበታል።
እንዲህም ይባላል፦ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው።”
5 ስለ ጽዮን ደግሞ እንዲህ ይባላል፦
“ይሄኛውም ሆነ ያኛው የተወለደው በእሷ ውስጥ ነው።”
ልዑሉ አምላክም አጽንቶ ይመሠርታታል።
6 ይሖዋ ሕዝቡን ሲመዘግብ
“ይህ በዚያ የተወለደ ነው” ብሎ ያስታውቃል። (ሴላ)
7 ዘማሪዎችና+ ጨፋሪዎች*+
“ምንጮቼ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛሉ”*+ ይላሉ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ለእኔ እውቅና ከሚሰጡት።”
^ ይህ ቃል ግብፅን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ኩሽን።”
^ ወይም “ክብ ሠርተው የሚጨፍሩ።”
^ ወይም “ለእኔ የሁሉ ነገር ምንጭ አንቺ ነሽ።”