ኢዮብ 30:1-31
30 “አሁን ግን ከእኔ በዕድሜ የሚያንሱ፣በእኔ ላይ ይስቃሉ፤+አባቶቻቸው መንጋዬን ከሚጠብቁ ውሾች ጋር እንዲሆኑፈቃደኛ አልነበርኩም።
2 የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይፈይድልኝ ነበር?
እነሱ ጉልበት ከድቷቸዋል።
3 ከችጋርና ከረሃብ የተነሳ ዝለዋል፤በወደመ እና ወና በሆነ ደረቅ ምድርያገኟትን ነገር ያላምጣሉ።
4 በቁጥቋጦዎች አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚል ተክል ይሰበስባሉ፤ምግባቸው የክትክታ ዛፍ ሥር ነው።
5 ከማኅበረሰቡ ተባረዋል፤+ሰዎችም ሌባ ላይ እንደሚጮኹ ይጮኹባቸዋል።
6 በሸለቆዎች* ተዳፋት ላይ፣መሬት ላይ ባሉ ጉድጓዶች ውስጥና በዓለቶች መካከል ይኖራሉ።
7 ከቁጥቋጦዎች ውስጥ ይጮኻሉ፤በሳማዎችም መካከል ይከማቻሉ።
8 ማመዛዘን የጎደላቸውና የአልባሌ ሰዎች ልጆች ናቸው፤ከምድሪቱ ላይ ተባረዋል።*
9 አሁን ግን በዘፈኖቻቸው ሳይቀር ይሳለቁብኛል፤+የእነሱ መሳለቂያ* ሆኛለሁ።+
10 ይጸየፉኛል፤ ከእኔም ርቀዋል፤+በፊቴ ከመትፋት ወደኋላ አይሉም።+
11 ምክንያቱም አምላክ ትጥቅ አስፈትቶኛል፤* ደግሞም አዋርዶኛል፤እነሱ በፊቴ እንዳሻቸው ይሆናሉ።*
12 በቀኜ በኩል እንደ አድመኛ ተነስተውብኛል፤እንድሸሽ አድርገውኛል፤በመንገዴም ላይ ለጥፋት የሚዳርግ መሰናክል አስቀምጠዋል።
13 መንገዶቼን ያፈርሳሉ፤መከራዬንም ያባብሳሉ፤+የሚገታቸውም የለም።*
14 ሰፊ ክፍተት ባለው ቅጥር እንደሚመጣ ሰው መጡ፤በፍርስራሹ መካከል እየገሰገሱ ገቡ።
15 በሽብር ተዋጥኩ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤የመዳን ተስፋዬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል።
16 አሁን ሕይወቴ* ከውስጤ ተሟጠጠች፤+የጉስቁልና ዘመን+ ያዘኝ።
17 ከባድ ሕመም በሌሊት አጥንቶቼን ይበሳል፤*+የሚመዘምዘኝ ሥቃይ እረፍት አይሰጠኝም።+
18 ልብሴ በታላቅ ኃይል ተበላሸ፤*እንደ ልብሴ አንገትጌ አንቆ ያዘኝ።
19 አምላክ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤አፈርና አመድ ሆንኩ።
20 እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+በፊትህ ቆምኩ፤ አንተ ግን ዝም ብለህ ታየኛለህ።
21 በጭካኔ በእኔ ላይ ተነሳህ፤+በእጅህ ብርታት አጠቃኸኝ።
22 ወደ ላይ አንስተህ በነፋስ ወሰድከኝ፤ከዚያም በአውሎ ነፋስ አንገላታኸኝ።*
23 በሕይወት ያለ ሁሉ ወደሚሰበሰብበት ቤት፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ አውቃለሁና።
24 ይሁንና የተሰበረ ሰው አደጋ ደርሶበት ለእርዳታ ሲጮኽ፣እጁን የሚያነሳበት ሰው አይኖርም።*+
25 መከራ ላይ ለወደቁ ሰዎች* አላለቀስኩም?
ለድሃውስ አላዘንኩም?*+
26 መልካም ነገር በተስፋ ብጠባበቅም ክፉ ነገር ደረሰ፤ብርሃን ብጠባበቅም ጨለማ መጣ።
27 ውስጤ ያለማቋረጥ ተናወጠ፤የጉስቁልናም ዘመን መጣብኝ።
28 በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ፤+ የፀሐይ ብርሃንም የለም።
በጉባኤ መካከል ቆሜ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ።
29 የቀበሮዎች ወንድም፣የሰጎንም ሴቶች ልጆች ባልንጀራ ሆንኩ።+
30 ቆዳዬ ጠቁሮ ተቀረፈ፤+ከሙቀቱ* የተነሳ አጥንቶቼ ነደዱ።
31 በገናዬ ለሐዘን ብቻ ዋለ፤ዋሽንቴም* ለለቅሶ ሆነ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “በደረቅ ወንዞች።”
^ ቃል በቃል “ተገርፈው (ተባረዋል)።”
^ ቃል በቃል “ምሳሌ፤ መተረቻ።”
^ ቃል በቃል “የደጋኔን አውታር አላልቶብኛል።”
^ ወይም “ልጓሙን ይፈታሉ።”
^ “የሚረዳቸው ሳይኖር መከራዬን ያባብሳሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ነፍሴ።”
^ ቃል በቃል “በሌሊት አጥንቶቼ ተቦርቡረዋል።”
^ “የደረሰብኝ ከባድ መከራ ሰውነቴን አበላሸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ “በኃይል አላትመህ በታተንከኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ቃል በቃል “በፍርስራሽ ክምር (ላይ እጁን የሚያነሳ አይኖርም)።”
^ ወይም “የመከራ ቀን ለገጠማቸው ሰዎች።”
^ ወይም “ነፍሴስ ለድሃው አላዘነችም?”
^ “ከትኩሳቱ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “እምቢልታዬም።”