ዘካርያስ 2:1-13
2 እኔም ቀና ብዬ ስመለከት በእጁ የመለኪያ ገመድ+ የያዘ ሰው አየሁ።
2 ከዚያም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅኩት።
እሱም “ወርዷና ርዝመቷ ምን ያህል እንደሆነ አውቅ ዘንድ ኢየሩሳሌምን ለመለካት እየሄድኩ ነው”+ ሲል መለሰልኝ።
3 እነሆም፣ ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ።
4 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ+ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች።+
5 እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’”+
6 “ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር ሽሹ”+ ይላል ይሖዋ።
“ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና”+ ይላል ይሖዋ።
7 “ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ።+
8 ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣* እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦+ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን* ይነካል።+
9 አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’+ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ።
10 “የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ፤+ እኔ እመጣለሁና፤+ በመካከልሽም እኖራለሁ”+ ይላል ይሖዋ።
11 “በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤+ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።
12 ይሖዋ ይሁዳን በተቀደሰው ምድር ላይ ድርሻው አድርጎ ይወርሰዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል።+
13 የሰው ልጆች ሁሉ፣* በይሖዋ ፊት ጸጥ በሉ፤ በቅዱስ መኖሪያው ሆኖ እርምጃ እየወሰደ ነውና።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ የመጀመሪያው ጽሑፍ “የዓይኔን ብሌን” የሚል ነበር። ሆኖም ሶፌሪም በመባል የሚታወቁት ጸሐፍት “የዓይኑን ብሌን” ብለው ቀየሩት።
^ ቃል በቃል “ከክብር በኋላ።”
^ ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”