በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዕድሜ፣ ብሔር ወይም ሃይማኖት ሳትለይ ሁሉንም ሰዎች ትረዳለህ?

የተቸገሩትን የሚረዱ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች

የተቸገሩትን የሚረዱ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች

በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎች ምግብና መጠለያ አጥተው ይቸገራሉ። አንዳንዶች ደግሞ የወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ሆኖ አይታያቸውም። ታዲያ እንዲህ ያሉ ሰዎችን መርዳታችን የአምላክን ሞገስና በረከት የሚያስገኝልን እንዴት ነው?

ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ?

“ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤ ላደረገውም ነገር ብድራት ይከፍለዋል።”—ምሳሌ 19:17

የተቸገሩትን መርዳት ሲባል ምን ማለት ነው?

ኢየሱስ የተናገረውን አንድ ምሳሌ እስቲ እንመልከት፤ ዘራፊዎች አንድን ሰው ደብድበው በሕይወትና በሞት መካከል ትተውት ሄዱ። (ሉቃስ 10:29-37) አንድ መንገደኛ በዚያ በኩል ሲያልፍ፣ ጉዳት የደረሰበትን ይህን ሰው አየውና ወስዶ ተንከባከበው። ሰውየው ሌላ ዘር ያለው መሆኑ ደግነት ከማሳየት ወደኋላ እንዲል አላደረገውም።

ይህ ደግ ሰው፣ ጉዳት የደረሰበትን ሰው ቁስል በማከምና የሚያስፈልገውን ነገር በመስጠት ሥቃዩ እንዲቀልለት አድርጓል።

ከዚህ ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን? ኢየሱስ ይህን ምሳሌ የተናገረው፣ የተቸገሩ ሰዎችን በምንችለው መንገድ ሁሉ መርዳት እንዳለብን ለማስተማር ነው። (ምሳሌ 14:31) ቅዱሳን መጻሕፍት፣ አምላክ በቅርቡ ድህነትንና ሥቃይን እንደሚያስወግድ ያስተምራሉ። ሆኖም አምላክ ይህን የሚያደርገው እንዴትና መቼ እንደሆነ ጥያቄ ይፈጠርብን ይሆናል። የሚወድህ ፈጣሪ ስላዘጋጀልህ በረከቶች በቀጣዩ ርዕስ ላይ እንመለከታለን።