በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሕይወት እና ሞት

ሕይወት

የሕይወት ትርጉሙ ምንድን ነው?

‘የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?’ ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል።

አምላክ ለእኔ ያለው ፈቃድ ምንድን ነው?

የአምላክን ፈቃድ ለማወቅ ራእይ ወይም ሌላ ለየት ያለ ምልክት ማየት ይኖርብሃል? መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ለዘላለም መኖር የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉ ሰዎች ለዘላለም እንደሚኖሩ ይናገራል። አምላክ እንድናደርግ የሚፈልጋቸውን ሦስት ነገሮች እንመልከት።

ነፍስ ምንድን ነው?

አንተ ከሞትህም በኋላ መኖሩን የሚቀጥል ረቂቅ ነገር በውስጥህ አለ?

“የሕይወት መጽሐፍ” ውስጥ የተጻፈው የእነማን ስም ነው?

አምላክ ለእሱ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን እንደሚያስታውሳቸው ቃል ገብቷል። ታዲያ የአንተ ስም “በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል”?

ሞት

ሰዎች የሚሞቱት ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ አጽናኝ ከመሆኑም በላይ ተስፋ ሰጪ ነው።

ስንሞት ምን እንሆናለን?

የሞቱ ሰዎች በአካባቢያቸው የሚከናወነውን ነገር ማወቅ ይችላሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ አስከሬን ስለ ማቃጠል ምን ይላል?

የሞቱ ሰዎችን አስከሬን ማቃጠል ተቀባይነት አለው?

ራሴን የማጥፋት ሐሳብ ሲመጣብኝ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳኝ ይችላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን የማጥፋት ሐሳብ ለሚመጣበት ሰው ምን ጠቃሚ ምክር ይዟል?

ሞትን ከመፍራት ነፃ መውጣት የምትችለው እንዴት ነው?

ሞትን ከልክ በላይ እንድትፈራ የሚያደርጉ ነገሮችን ማስወገድ በሕይወትህ ደስተኛ እንድትሆን ይረዳሃል።

ሞት አፋፍ ላይ ደርሰው የተመለሱ ሰዎች እንዳጋጠማቸው የሚናገሩት ትክክል ነው?

ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት የሚጠቁሙን ነገር አለ? ስለ አልዓዛር ትንሣኤ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ስለዚህ ጉዳይ የሚነግረን ነገር አለ።

የምንሞትበት ቀን አስቀድሞ ተወስኗል?

መጽሐፍ ቅዱስ “ለመሞትም ጊዜ አለው” ሲል ምን ማለቱ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው ከሥቃይ ለመገላገል ሲባል እንዲሞት ማድረግን በተመለከተ ምን ይላል?

አንድ ሰው የማይድን በሽታ ቢይዘውስ? ሕይወቱን ለማራዘም ማንኛውም መሥዋዕትነት መከፈል አለበት?

ሰማይና ሲኦል

ሰማይ ምንድን ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል ሦስት ዋና ዋና ትርጉሞች አሉት።

ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?

ብዙ ሰዎች፣ ጥሩ ሰዎች በሙሉ ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ያስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ያስተምራል?

እውነት ሲኦል አለ? የመጽሐፍ ቅዱሱ ሲኦል ምንድን ነው?

ብዙ ሰዎች፣ ሲኦል ክፉ ሰዎች በእሳት የሚቀጡበት ዘላለማዊ መሠቃያ ቦታ እንደሆነ ያምናሉ። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሎ ያስተምራል?

ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው?

ጥሩ ሰዎች ወደ ሲኦል ይገባሉ? አንድ ሰው ከሲኦል መውጣት ይችላል? ሲኦል ለዘላለም ይቀጥላል? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

የእሳት ሐይቅ ምንድን ነው? ገሃነም ነው? ወይስ ሲኦል?

ኢየሱስ “የሲኦል መክፈቻ” አለው፤ ነገር ግን የእሳት ሐይቅ መክፈቻ አለው?

ሀብታሙ ሰውና አልዓዛር እነማን ናቸው?

ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ ጥሩ ሰዎች ወደ ሰማይ እንደሚሄዱና መጥፎ ሰዎች በሲኦል እሳት እንደሚሠቃዩ ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንጽሔ ይናገራል?

የዚህ ትምህርት አመጣጥ ያስገርምህ ይሆናል።

እንስሳት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ የቤት እንስሳት ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ አይናገርም፤ ይህ የሆነበት በቂ ምክንያት አለ።

የሞቱ ሰዎች ያላቸው ተስፋ

ትንሣኤ ምንድን ነው?

ወደፊት እነማን ከሞት እንደሚነሱ ስታውቅ ልትገረም ትችላለህ።