የአጠቃቀም ውል
እንኳን ደህና መጣህ!
ይህ ድረ ገጽ የተዘጋጀው ስለ አምላክ፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስና ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ይበልጥ እንድታውቅ ለመርዳት ታስቦ ነው። የምትፈልገውን ርዕስ ማንበብ፣ ቪዲዮ መመልከት እንዲሁም የፈለግከውን ነገር ማውረድ ትችላለህ። ሌሎች ሰዎችም ከድረ ገጻችን እንዲጠቀሙ እንፈልጋለን፤ ሆኖም በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉትን መረጃዎች በሌላ ድረ ገጽ ወይም አፕሊኬሽን አማካኝነት እንዲሰራጩ አታድርግ። ከታች ባለው የአጠቃቀም ውል ላይ በተጠቀሰው መሠረት ከዚህ ድረ ገጽ ያገኘኸውን ነገር ለሌሎች ማካፈል ከፈለግክ ድረ ገጹን እንዲጎበኙ መጋበዝ ትችላለህ።
የቅጂ መብት
2024 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።
ይህን ድረ ገጽ ያዘጋጀውም ሆነ ክትትል የሚያደርግለት Watchtower Bible and Tract Society of New York, Inc. (“Watchtower”) ነው። ሌላ መግለጫ ካልተሰጠ በቀር በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኘው ማንኛውም ጽሑፍና መረጃ Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania, Inc. (“Watch Tower”) የተባለው ድርጅት አእምሯዊ ንብረት ነው።
የንግድ ምልክቶች
Adobe የሚለው መጠሪያና ዓርማው እንዲሁም Acrobat የሚለው መጠሪያና አርማው የAdobe Systems Incorporated የንግድ ምልክቶች ናቸው። Apple፣ iTunes እና iPod ደግሞ የApple Inc. የንግድ ምልክቶች ናቸው። Microsoft የሚለው መጠሪያና ዓርማው እንዲሁም Microsoft Office እና Microsoft Office 365ን ጨምሮ ማንኛውም የማይክሮሶፍት ሶፍትዌርና ምርቶች የMicrosoft Inc. የንግድ ምልክቶች ናቸው። Android የGoogle LLC የንግድ ምልክት ነው። የAndroid ሮቦት Google ከሚሠራቸውና ከሚያጋራቸው ሥራዎች የሚባዛ ወይም ተሻሽሎ የሚቀርብ ሲሆን በCreative Commons 3.0 Attribution License ላይ በተገለጸው ስምምነት መሠረት ጥቅም ላይ ይውላል። (https://creativecommons.org/licenses/by/3.0/us/) በድረ ገጹ ላይ የሚገኙ ሌሎች የንግድ ምልክቶችና በሕግ የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶች የባለቤቶቻቸው ንብረቶች ናቸው።
የአጠቃቀም ውል እና ድረ ገጹን ለመጠቀም የሚሰጥ ፈቃድ
ይህን ድረ ገጽ በምትጠቀምበት ጊዜ የምትመራው በዚህ የአጠቃቀም ውል ነው። ይህን ድረ ገጽ መጠቀምህ በዚህ ድረ ገጽ ላይ በተገለጸው የአጠቃቀም ውልም ሆነ በተጨማሪ የአጠቃቀም ውሎች (በጥቅሉ፣ “የአጠቃቀም ውል”) መሠረት ለመመራት ሙሉ በሙሉ መስማማትህን ያሳያል። በዚህ የአጠቃቀም ውል ወይም በውሉ ላይ ከተጠቀሱት ስምምነቶች ውስጥ በአንዱም ቢሆን የማትስማማ ከሆነ ድረ ገጹን መጠቀም የለብህም።
ድረ ገጹን በተገቢው መንገድ መጠቀም ሲባል ምን ነገሮችን ይጨምራል? ከታች ከተገለጹት ገደቦች ሳታልፍ የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ትችላለህ፦
-
የቅጂ መብቱ የWatch Tower የሆኑ በድረ ገጹ ላይ የሚገኙ ሥዕሎችን፣ የኤሌክትሮኒክ ጽሑፎችን፣ ሙዚቃዎችን፣ ፎቶዎችን፣ ጽሑፎችን ወይም ቪዲዮዎችን ለግልና ከንግድ ውጭ ለሆነ ዓላማ ለመጠቀም መመልከት፣ ማውረድና ማተም ትችላለህ።
-
በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኙ ጽሑፎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም የኦዲዮ ፕሮግራሞችን አውርደህ ወይም ሊንኩን ወስደህ ለሌሎች መላክ ትችላለህ።
የማይፈቀዱ ነገሮች፦
-
ከዚህ ድረ ገጽ ላይ የተወሰዱ ሥዕሎችን፣ የኤሌክትሮኒክ ጽሑፎችን፣ የንግድ ምልክቶችን፣ ሙዚቃዎችን፣ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም ሐሳቦችን ኢንተርኔት (ፋይሎችንና ቪድዮዎችን ማጋራት የሚቻልባቸውን ድረ ገጾችና ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ጨምሮ ማንኛውም ድረ ገጽ) ላይ ፖስት ማድረግ።
-
በድረ ገጹ ላይ የሚገኙ ሥዕሎችን፣ የኤሌክትሮኒክ ጽሑፎችን፣ የንግድ ምልክቶችን፣ ሙዚቃዎችን፣ ፎቶዎችን፣ ጽሑፎችን ወይም ቪዲዮዎችን ከሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች ጋር በማያያዝ ወይም በዚያ ውስጥ በማካተት ማሰራጨት (ይህም በድረ ገጹ ላይ የሚገኙ ነገሮችን የሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች እንዲጠቀሙባቸው ሲባል ሰርቨር ላይ መጫንን ይጨምራል)።
-
በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሥዕሎች፣ የኤሌክትሮኒክ ጽሑፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ ሙዚቃዎች፣ ፎቶዎች፣ ጽሑፎች ወይም ቪዲዮዎች በመገልበጥ፣ በማባዛት፣ በመቅዳት፣ በማሰራጨት ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ (ትርፍ የሚገኝበት ባይሆንም እንኳ) ለንግድ ወይም ገንዘብ ለማግኘት መጠቀም።
-
ከዚህ ድረ ገጽ ላይ በማንኛውም መልኩ መረጃዎችን፣ HTML ፋይሎችን፣ ሥዕሎችን ወይም ጽሑፎችን ለመሰብሰብ፣ ለመቅዳትና ለማውረድ እንዲሁም ኤክስትራክት፣ ሃርቨስት ወይም ስክሬፕ ለማድረግ የሚያገለግሉ የሶፍትዌር አፕሊኬሽኖችን፣ መሣሪያዎችን ወይም ቴክኒኮችን አዘጋጅቶ ማሰራጨት። (ይህ በድረ ገጹ ላይ ከሚገኙ ሁሉም ሰው ሊጠቀምባቸው ከሚችል ክፍሎች ላይ እንደ EPUB፣ PDF፣ MP3 እና MP4 ያሉ ኤሌክትሮኒክ ፋይሎችን ለማውረድ ተብለው የተዘጋጁ ነፃ የሆኑና ለንግድ ዓላማ የማይውሉ አፕሊኬሽኖችን ማሰራጨትን አይጨምርም)
-
ድረ ገጹን ወይም ድረ ገጹ የሚሰጠውን አገልግሎት አላግባብ መጠቀም፤ ለምሳሌ ድረ ገጹን ወይም ድረ ገጹ የሚሰጠውን አገልግሎት ማስተጓጎል ወይም በግልጽ ከተቀመጠው መንገድ ውጪ ድረ ገጹን ወይም ድረ ገጹ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመጠቀም መሞከር።
-
ድረ ገጹን በሚጎዳ ወይም ሊጎዳው በሚችል እንዲሁም ድረ ገጹ እንዳይሠራ ወይም ወደ ድረ ገጹ መግባት አስቸጋሪ እንዲሆን በሚያደርግ መንገድ ድረ ገጹን መጠቀም፤ አሊያም በምንም መንገድ ቢሆን ሕገ ወጥ ወይም ጎጂ ለሆነ ዓላማ ብሎም ለወንጀልና ለማጭበርበር አሊያም ከዚህ ጋር ግንኙነት ላለው ተግባር መጠቀም።
-
ድረ ገጹን ወይም በድረ ገጹ ላይ የሚገኙትን ሥዕሎች፣ የኤሌክትሮኒክ ጽሑፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ ሙዚቃዎች፣ ፎቶዎች፣ ጽሑፎች ወይም ቪዲዮዎች ከሽያጭ ወይም ከግብይት ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ተግባር መጠቀም።
ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች
በድረ ገጹ ላይ የሚገኘው ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች የሚለው ክፍል (“Medical Section”) ዓላማ ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ማቅረብ ብቻ ነው፤ የምክር አገልግሎት አይሰጥም፤ የሕክምና ባለሙያዎች የሚያደርጉትን ምርመራ እንዲሁም የሚሰጡትን ምክር ወይም ሕክምና የሚተካም አይደለም። ይህ ክፍል በሥሩ ከተጠቀሱት ምርመራዎች፣ የሕክምና ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶች፣ የሕክምና ዓይነቶች፣ አስተያየቶች ወይም ሌሎች መረጃዎች መካከል የትኛውንም የተሻለ እንደሆነ አድርጎ አይጠቅስም ወይም ሰዎች እንዲጠቀሙበት አያበረታታም።
ከአንድ ዓይነት ሕመም ወይም ሕክምና ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ ካለህ የሕክምና ባለሙያዎችን ወይም የሕክምና አገልግሎቶችን ለመስጠት ብቁ የሆኑ ሌሎች ግለሰቦችን ማማከርህ ምንጊዜም የተሻለ ነው።
በድረ ገጹ ላይ ባለው ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች በሚለው ክፍል ሥር ትክክለኛና ወቅታዊ የሆኑ የሕክምና መረጃዎችን ለማካተት ተሞክሯል። ይሁንና በዚህ ክፍል ሥር የሚገኘው መረጃ በሙሉ “እንዳለ ሆኖ” የተቀመጠ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተቀመጠ የዋስትና ማረጋገጫ የለም። ይህ ድረ ገጽ ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች ከሚለው ክፍል ጋር በተያያዘ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዋስትና ማረጋገጫዎች አይሰጥም፤ ይህም ደረጃውን የጠበቀ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በተዘዋዋሪ የተገለጸ ማረጋገጫንና ለአንድ ዓይነት ዓላማ ብቁ መሆኑን የሚገልጽ ማረጋገጫን ጨምሮ ሌሎች ማረጋገጫዎችን ይጨምራል። ይህ ድረ ገጽ ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች በሚለው ክፍል ሥር ለሚቀርቡት መረጃዎች ተአማኒነት፣ ትክክለኝነት፣ ወቅታዊነት፣ ጠቃሚነት ወይም ሙሉነት ማረጋገጫ አይሰጥም። ድረ ገጹ ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች በሚለው ክፍል ሥር ለሚኖር ስህተት ወይም የመረጃ መጓደል ተጠያቂ አይደለም። በዚህ ክፍል ባሉት መረጃዎች ላይ መተማመን ወይም አለመተማመን የእያንዳንዱ ግለሰብ ምርጫ ነው። ይህ ድረ ገጽ ከሕክምና ጋር የተያያዙ መረጃዎች የሚለውን ክፍል በመጠቀም ወይም መጠቀም ባለመቻል ምክንያት ለሚመጣ ማንኛውም ክስ ወይም በሰዎች ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት (ይህም ወዲያው ወይም ዘግይቶ የሚከሰትን ጉዳት፣ በራስ ላይ የሚደርስን ጉዳት/ሞት፣ ማግኘት የሚገባውን ትርፍ ማጣትን ወይም በመረጃ መጓደል ወይም በሥራ መስተጓጎል ምክንያት የሚመጣ ጉዳትን እና ሌሎች ነገሮችን ይጨምራል) ተጠያቂ አይሆንም፤ እነዚህ ክሶች በዋስትና ማረጋገጫ፣ በውል፣ በጉዳት ተጠያቂነት አሊያም በሌላ በማንኛውም ከሕግ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ላይ የተመሠረቱ ሆኑም አልሆኑ እንዲሁም ድረ ገጹ ስለ ጉዳዩ የሚያውቀው ነገር ኖረም አልኖረ ድረ ገጹ ተጠያቂ አይሆንም።
የዋስትና ማረጋገጫን አለመስጠት እና የተጠያቂነት ገደብ
ይህ ድረ ገጽና በዚህ ድረ ገጽ አማካኝነት የሚሰራጩት መረጃዎች፣ በድረ ገጹ ላይ የሚወጡ ነገሮችና አገልግሎቶች በWatchtower በኩል የሚቀርቡት “እንዳሉ ሆነው” ነው። Watchtower በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተቀመጠ የዋስትና ማረጋገጫ አይሰጥም።
Watchtower ድረ ገጹ ከቫይረስም ሆነ ከሌሎች ጎጂ ነገሮች ነፃ እንደሆነ ማረጋገጫ አይሰጥም። Watchtower በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኝን አገልግሎት፣ መረጃ፣ በድረ ገጹ ላይ የሚወጡ ነገሮች ወይም በዚህ ድረ ገጽ አማካኝነት የሚገኙ ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም ለሚመጣ ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ አይሆንም፤ ይህም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ፣ በአጋጣሚ፣ በቅጣት እንዲሁም በተያያዥነት የሚመጡ ጉዳቶችን (ማግኘት የሚገባን ትርፍ ማጣትን ጨምሮ) እና ሌሎች ነገሮችን ያጠቃልላል።
የአጠቃቀም ውሉን ማፍረስ
በዚህ የአጠቃቀም ውል ውስጥ የተገለጹት የWatchtower ሌሎች መብቶች እንዳሉ ሆነው በውሉ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ስምምነት ብታፈርስ Watchtower ተገቢ መስሎ የታየውን እርምጃ ሊወስድ ይችላል፤ ይህም ድረ ገጹን የመጠቀም መብትህን ማገድን፣ ድረ ገጹን እንዳትጠቀም መከልከልን፣ የአንተን IP አድራሻ የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች ድረ ገጹን ማግኘት እንዳይችሉ ማገድን፣ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥህ ድርጅት ድረ ገጹን ከመጠቀም እንዲያግድህ መጠየቅን እና/ወይም ሕጋዊ እርምጃ መውሰድን ይጨምራል።
ለውጦች
Watchtower ይህን የአጠቃቀም ውል አልፎ አልፎ ሊያሻሽለው ይችላል። የተሻሻለው የአጠቃቀም ውል በድረ ገጹ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ድረ ገጹን የሚጠቀሙ ሁሉ የተሻሻለውን ውል ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። እባክህ ወቅታዊ የሆነውን ውል በደንብ ማወቅ እንድትችል ይህን ገጽ በየጊዜው ተመልከተው።
ሕግ እና ሥልጣን
የምትኖርበት ግዛት ወይም አገር ሕግ ከዚህ ጋር የሚስማማ ሆነም አልሆነ፣ ይህ የአጠቃቀም ውል የሚተረጎመውና ተፈጻሚ የሚሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በሆነው በኒው ዮርክ ሕግ መሠረት ነው። ከዚህ የአጠቃቀም ውል ጋር የተያያዘ ማንኛውም ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰደው ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የኒው ዮርክ ግዛት ላይ ሥልጣን ባለው የግዛቱ ወይም የፌዴራል ፍርድ ቤት መሆን ይኖርበታል።
ስምምነቶቹ የሚታዩት በተናጠል ነው
በአጠቃቀም ውሉ ውስጥ ከተጠቀሱት ስምምነቶች መካከል አንዱ፣ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ውድቅ ቢሆን፣ ተቀባይነት ቢያጣ አሊያም ተፈጻሚ መሆን እንደማይችል ወይም ሕጋዊ እንዳልሆነ ቢወሰን በውሉ ውስጥ የተጠቀሱት የተቀሩት ስምምነቶች የጸኑ እንደሆኑ ይቀጥላሉ። Watchtower በአጠቃቀም ውሉ ውስጥ የተጠቀሱትን ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ሳያደርግ ቢቀር እነዚህን ስምምነቶች ወይም ስምምነቶቹን የማስፈጸም መብቱን በገዛ ፈቃዱ ትቷል አያስብለውም።
አጠቃላይ ስምምነት
ይህ የአጠቃቀም ውል፣ ድረ ገጹን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ በአንተ እና በWatchtower መካከል የተደረገውን አጠቃላይ ስምምነት የያዘ ነው፤ እንዲሁም ይህን ድረ ገጽ ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የተደረጉ ስምምነቶችን የሚተካ ነው።